እርስዎ ወይም እንስሶችዎ ድንገተኛ እና ምክንያት የሌለው ህመም ወይም መመረዝ ምልክት ካዩ ሃኪምዎ ጋር ወይም የእንስሳ ሃኪምዎ ጋር ይደውሉ
አልጌዎች በሃይቅ ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን ነፍስ ያላቸው ፍጥረቶች ሲሆኑ ልክ እንደ እጽዋት ለማደግ የጸሃይ ብርሃን ይጠቀማሉ። አልጌዎች በሃይቅ ውስጥ ላሉ አሳዎች ወይም እንስሳት ጠቃሚ ምግብ ናቸው። ነገር ግን አንዳንድ አልጌዎች ለሰዎችና ለእንስሳት ጎጂ የሆነ መርዝ ያመነጫሉ።
መርዛማ አልጌ ውሃው ላይ ቀለም የተደፋ የሚመስል እይታ ወይም ትናንሽ ነጥቦች ወይም ስብስቦች ይመስላሉ።
አብዛኛውን ጊዜ ፈዛዛ አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ- አረንጓዴ ሲመስሉ አንዳንድ ጊዜም አረንጓዴ፥ ቢጫ፥ ወይም ቡናማ ቀለም አላቸው። ተጨማሪ ምስሎችን ለማግኘት https://www.nwtoxicalgae.org/Gallery.aspx። እንደዚህ አይነት የሚመስል አልጌ ካዩ፥ ደህንነትዎን ይጠብቁ እና ወደ ሃይቁ ውስጥም አይግቡ!
አልጌው ጥቅጥቅ ያለ ሽፋን ወይም ገመድ መሳይ ነገር ኖሮት በእጅዎ ማንሳት የሚችሉት ከመሰለውዎ ፥ ይህ የተለየ አይነት አልጌ ነው። መርዛማ ነገሮችን አያመነጭም።
በዋሺንግተን ግዛት ውስጥ የትኞቹ ሃይቆች መርዛማ አልጌ እንዳላቸው ለማወቅ www.nwtoxicalgae.org ይጎብኙ። በቀኝ በኩልም የሃይቆችን ዝርዝር ይመልከቱ። በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉ ሃይቆች በቅርቡ ከእነርሱ በተወሰደው ናሙና መሰረት አስተማማኝ ያልሆነ የመርዝ ክምችት ተገኝቶባቸዋል።
የተጻፈው ቀይ ጽሁፍ የሚከተለውን የሚል ከሆነ “no lake is above guidelines” (ምንም አይነት ሀይቅ ከመመሪያው በላይ አይደለም), በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይህ ሀይቅ ምንም አይነት መርዛማነት ከናሙናቸው ላይ አልተገኘም ማለት ነው።